ውድ አንባቢዎች – My Review

ይህንን ሪቪው ለናንተ ሳቀርብ   አላማዬ በአማርኛ የተፃፉ ፅሁፎች በኢንተርኔትና በድረገፆች እንደልብ በገፍ እንዲገኙ የበኩሌን አስተዋፅኦ ለማድረግ ነው።  ለቋንቋችንና ለታሪካችን  ባለኝ ፍቅር በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት በብዙ ምእተ አመታት የበለፀገው ታሪካችን ብቻ ሳይሆን ስነ ፅሁፍና  ቋንቋችን የበለጠ ከፍ ወዳለ ደረጃ እንዲደርስ ድርሻዬን ለማበርከት እሞክራለሁ።  ይህ ሪቪው በተለያዩ አርእስቶች ላይ ሰፋ መድረክ ለመስጠት ቅኔዎችን፣ግጥሞችን ፣ትውፊቶችንና ሌሎችንም እንደሚያሰባስብ ሁሉ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ  ብሄር ብሄረሰቦች ከጥንት አባቶቻችን በቃል እያተላለፉልን እኛ ጋ ደርሰው  ዛሬም የሚነገሩ ልዩ ልዩ ምሳሌያዊ  አባባሎችንና፣ተረቶችን እንዳይጠፉ ለማድረግ ጥረት ያደርጋል።  

 በግእዝ ፊደላት ለመፃፍ በተሰራው በዚህ ኮምፒውተር  በመጠቀም በቀላሉ

  • ለመፃፃፍና ለመማማር
  • ፋይል ለማድረግ
  • መረጃ ለመለዋወጥና ለማስተላለፍ የሚቻልበት ዘዴ ተቀይሷል።

ይህንን ልዩ የፈጠራ ውጤት እውን ለማድረግ ባደረግነው ጥናት ስለቋንቋችን የደረስንበትን ግኝት እንዲሁም ለጋራ ታሪካችን ያደረገውን አስተዋፅኦ  ከአንባቢዎቼ ለመካፈል መድረኩን እጠቀማለሁ። የአማርኛ ፅሁፎች ክምችት በኢንተርኔት ውስጥ እንዲበረክት የሚያግዝ የአማርኛ ላይብረሪ እንዲኖር የራሴን ድርሻ አበረክታለሁ። ቋንቋችንንን ማጥናትና ማበልፀግ ሁላችንም ልንተጋበት የሚገባ መሆኑን አምናለሁ። ለዚህም የናንተ የአንባቢዎቼ ድጋፍና አስተዋፅኦ እንደማይለየኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

ገነት አየለ

Devoted to our history and language, my aim is to make Amharic texts available on the Internet, and contribute to the advancement of our literature, linguistics and  historical heritage.  The domain of the review is deliberately broadly conceived, to promote  Ethiopian multicultural heritage  in it’s diversity by sharing poems, short stories and folklorics  from different parts of  Ethiopia.This review will contribute to Education and Communication in Ethiopia by making available the tools we have built to make  amharic an Internet language :

  • easy to write
  • easy to file
  • easy to transmit

I shall share with  the readers our discoveries about the language itself and its contribution to Ethiopian history.

I shall promote the building of an Ethiopian library for amharic content.

GUENET AYELE

አንድ ቁልፍ ብቻ በመጫን የተፃፉ ግጥሞች
Poems written with a one keystroke

ከዚህ በታች በቁልፍ ሰሌዳው ላይ ያሉትን ፊደላት ብቻ በመጠቀም የተፃፉ ግጥሞች ለአብነት ያህል ተቀምጠዋል። እነዚህ ከቁልፍ ሰሌዳው ለመተዋወቅና በፍጥነት ለመፃፍ ልምምድ ለማድረግ ይረዳሉ። የፊደሎቹ አቀማመጥ የላቲን ፊደሎችን ከግምት ሳያስገባ በአዲስ አቀማመጥ የተዘጋጀ ነው። ይህም ኮምፒውተሩ ኢትዮጵያዊ መልክ ይዞ የራሳችን የሆነ አዲስ የፈጠራ ውጤት መሆኑን ያመላክታል።

The following poems are written with characters accessible in one keystroke using our keyboard. This will help to get acquainted to the keyboard by practicing the position of the characters.

ተገላገይ

ደጅሽ የበቀለው ምን አይነት ተክል ነው
አያደርቅ አይለመልም ከአመት አመት ያው ነው
እርባና ከሌለው ነቅለሽ ተገላገይ
ከትከሻሽ ይውረድ ወስኝ አታወላውይ

ተረት ተረት የመሰረት

ተረት ተረት
የላም በረት
አንድ ወፍ ነበረች
እሽሽሽሽሽሽሽ
እሽ  ስትላት በረረች !!!

ሰው ማለት

አላህን አመስጋኝ በቀን ሆነ በመአልት
ምስጋናው አይቀርም ምንም ባይሆንለት
የማያወላውል በመከራ ሰአት
በእምነት  የከበረ ይህ ነው ሰው ማለት

ህብረ ቀለም

እናት አለም ወንዝሽና ተራራው
ውል እያለኝ ላላገኘው
ጋራና መስክ አረህ ቀየው
ትዝ እያለኝ ጠረን ሽታው
የምናፍቅ የምመኝሽ
ሰላም ልበልሽ ውድ  ልጅሽ
ግን አልባክን እባክሽን በስምሽ ልጠራ
አትተይብኝ የተቀበልሽውን አደራ
እርመ በላ ሆነሽ በሰማይ ከማስጠይቅሽ
ትንታግ ሆነሽ አታብግኝኝ ግፍ ይቅርብሽ
አልባክን አልንከራተት ልክረም ከእቅፍሽ
ይህ ነህ አትበይኝ በወገን አደላድለሽ
ያ ነህ አትበይኝ በነገድ አራርቀሽ
አገር ነሽና እንደጥንት እንደልማድሽ
ደምቀሽ  ብቅ በይልኝ እማማ በህብረ ቀለምሽ
ባእድ አገር ስንከራተት
መከራና  ጭንቀት
አስረውኝ ባንድነት
ስማማልልብሽ ስባዝት
ጥመለመል  ርበተበት
አድባር አውጋር ባይደርስልኝ
እነ ስም አይጠር ተማምለው ከድተውኝ
እማማ እናት አለም አንችን ግን ልጥራሽ
ብቅ በይልኝ እንደልማድሽ
እንደ ወርቅብረቅርቅ ወንዝሽ
እንደ አልማዝ ያብ ሀይቅሽ
ቀስተ ደመናን ታጥቀሽ
በህብረ ቀለም ደምቀሽ
ይህ ነህ አትበይኝ በወገን አደላድለሽ
 ያ ነህ አትበይኝ በነገድ አራርቀሽ
 አገር ነሽና እንደጥንት እንደልማድሽ
ተውበሽ  ብቅ በይልኝ እማማ በህብረ ቀለምሽ

Get your amharic laptop now

A powerful Fujitsu with an amharic keyboardThis FUJITSU Notebook LIFEBOOK A555G is a high-end laptop designed for nomad everyday work.


Its Intel® CoreTM i5-5200U processor is the fifth generation of Intel chips, specifically created to reduce the energy consumption of the device. You can work longer while on battery with no drop in the overall performance of your applications.


It comes with an AMD RadeonTM R7 M260 graphics card with 2GB dedicated memory, enabling full HD display for an optimal visual rendition.


You will experience no shortage of memory with its 4GB RAM, and 1TB Hard Disk Drive memory.


This great hardware runs a customised version of Ubuntu, enabling for full support of both English and Amharic languages.


Facebook
Special offer!

Subscribe to our newsletter