Methodology

በአዲሱ የፈጠራ ውጤታችን ለወደፊት እርምጃችን አዲስ መንገድ

ጥንታዊ ታሪካችንና  ባህላዊ እሴታችን የበለፀገ እንደመሆኑ ሁሉ በአይነቱም የተለያየ ነው።  ለኛ የምንኮራበትን ማንነታችን የተቀረፀበት የብሔራዊ ኩራታችን ምንጭ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃም ትኩረትን የሳበ ነው።

ይሁንና በዚህ የኢንተርኔትና የኮምፒውተር ዘመን ከእውነታው ጋር አብሮ ለመሄድ የሚያስችል የተሻሻለ፣ ቀላልና አመቺ የአጻጻፍ ስርአትን ያላዳበረ ቋንቋ ቀስ በቀስ ቦታውን ለሌሎች ለቆ መክሰሙ የማይቀር ነው።

እንደሚታወቀው በቋንቋችን የተፃፉ ኢንተርኔት ላይ የሚገኙ  መጽሐፎች፣መረጃዎች፣ዲክሽነሪዎችና የመሳሰሉት የመማር ማስተማሪያ መሳሪያዎች ሁሉ በኢንተርኔት ላይ ያላቸው ቁጥር በጣም ውስን ነው። ትምህርትና እውቀትን በቀላሉ ልናገኝባቸው የምንችለው  እንደዊኪፔድያና የመሳሰሉ በማንኛውም አርእስት ላይ የተወሰነም ቢሆን መረጃ ሊሰጡ የሚችሉ መድረኮች ጥቂት ናቸው። በአማርኛ ብቻ ሳይወሰን በሌሎችም የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ አገርኛ ቋንቋዎቻችን ላይ ችግሩ የባሰ  ነው።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ የበኩላችንን አነስተኛ ድርሻ ለማበርከት ጥንታዊውንና፣ብቸኛውን የምንኮራበትን ፊደላችንን በመጠቀም ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራውን የአማርኛና የእንግሊዝኛ ላፕቶፕ ኮምፒውተር  ለገበያ ስናቀርብላችሁ  ከፍተኛ ደስታና ኩራት ይሰማናል።

በግዕዝ ፊደሎች የተዘጋጀ የቁልፍ ሰሌዳ የተቀረፀበት ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ  አዲሱ ኮምፒውተር የቋንቋና ፊደሎቻችንን ታሪካዊ መሰረት በማይንድ መልኩ በጥንቃቄ ተዘጋጅቶ በቀላል ዘዴ ለመፃፍ እንዲቻል ተገቢውን መፍትሔ በማካተት የቀረበ ነው።የሰራነው ኮምፒውተር የተመረኮዘበት መሰረተ ሃሳብ አማርኛን ባልተወሳሰበ መንገድ ብዙ ቁልፎችን መነካካት ሳያስፈልግ መፃፍ መቻል ነው።

ይህን እውን ለማድረግ የኮምፒውተራችን መተግበሪያ (software) የተደራጀበት አርክቴክቸር እንደዚሁ በዘፈቀ የተሰራ ሳይሆን በቋንቋው ላይ በተደረገ ጥናት ላይ የተመረኮዘ ነው።  የፊደሎቹን አቀማመጥ ለመወሰን ባደረግነው ጥናት 11ሚሊየን ያህል የአማርኛ ቃላትን ከተለያዩ ፅሁፎች ላይ ለአብነት ወስደን በአንድ የመለያ ቋት ውስጥ ካስገባን በኋላ በድግግሞሻቸው መጠን ቅደም ተከተል አውጥተን ለይተናቸዋል። ከዚያም የድግግሞሻቸው መጠን ከፍተኛ የሆነውን የፊደላት ስብስብ  በቁልፉ ሰሌዳ ላይ እንዲቀመጡ አድርገናል።  በጥናቱ መሠረት ባወጣነው ዳታ በአጠቃቀም የድግግሞሻቸው መጠን ከፍተኛ የሆነውን ፊደላት ለይተን ማውጣት ብቻ ሳይሆን በቁልፍ ሰሌዳው ላይ ለመተየብ አመቺ እንዲሆኑ የት ቢቀመጡ ይሻላል የሚለውንም  ለመወሰን ረድቶናል።

በዚህ አይነት ፍፁም አገርኛ ሆኖ የተዘጋጀው ልዩ የቁልፍ ሰሌዳ በፊደል ገበታው ላይ ካሉት ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት ፊደሎች ቢያንስ አንዱ በቁልፍ ሰሌዳው ላይ እንዲቀመጥ ለማድረግ አስችሎናል።  ይህም ማለት የኩዌርቲን የቁልፍ ሰሌዳ ስንጠቀም እንደምናደርገው ሁለት ሶስት ቁልፎችን በመነካካት አንድ ፊደል ለመፃፍ የምንሰራው የጣት ጂምናስቲክ ይቀርልናል ማለት ነው። የመረጥናቸው ስብስቦች ብዙ  ጊዜ የምንጠቀምባቸውን ፊደሎች ስለያዙ  አንድ ቁልፍ በመጫን ብቻ ለመፃፍ የምንችልበት ሁኔታ ተመቻችቷል።

አዲሱ ኮምፒውተር የማንበብና የመፃፍ ክህሎትን ለማሳደግ በተለይም ለህፃናትና ለአዲስ ጀማሪዎች በቀላሉ ለመፃፍ እንዲችሉ የሚረዳ ነው። ህፃናት በሚማሩት ቋንቋ ላይ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ ዘመናዊ የትምህርት መሳሪያዎችንም ለማደራጀት በር ይከፍታል።ለዚህም አብነት እንዲሆን በቁልፍ ሰሌዳው ላይ ቅድሚያ የተሰጣቸውን ፊደሎች  ስብስብ ብቻ በመጠቀም አርፍተ ነገሮችን ለመፃፍ ስለሚቻል የነዚህን ቃላትና አርፍተ ነገሮች  የያዘ መዝገበ ቃላት  ለተጠቃሚዎች አቅርበናል። በተጨማሪም የተለያዩ የአማርኛ ጽሑፎችን ለማከማቸትና ለማሰራጨት የሚያገለግል ሪቪው አዘጋጅተናል። ይህ ማህደረ ብዙ መረጃ ሰጪ ሪቪው  በአለም ዙሪያ የሚገኙ ፈላጊዎች ሁሉ ተጠቃሚ  ይሆኑበታል።

በቁልፍ ሰሌዳው ላይ 233ቱም የግዕዝ ሆሄያት ከነተከታዮቻቸው ማስቀመጥ ባይቻልም ከታሪካዊ ፊደሎቻችን አንዱም እንኳ አስፈላጊ አይደለም ተብሎ መቅረት አይችልም። ሁሉም አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው።  በአንፃሩ ደግሞ ቋንቋው ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚሄድ  የመግባቢያና የመላላኪያ መሳሪያ እንዲሆን መሻሻል ይጠበቅበታል። ቋንቋው ወደፊት በተራመደ ቁጥር የአፃፃፍ ሥርዓቱም ተሻሽሎ የቋንቋውን እርምጃ መከተል ይገባዋል። ለዚህ መፍትሄው ምንድነው?  ለምሳሌ “ሀ” የሚለውን ድምፅ ለመፃፍ ሰባት አማራጮች አሉን።( ሀ ሐ ኀ ሃሓ ኃ ኻ ) እነዚህን ሁሉ በቁልፍ ሰሌዳው ላይ ማስቀመጥ አይቻልም።ልንጥላቸውም አይገባም ። ስለዚህ  ፊደሎቹ ጥንታዊ ቅርፃቸውንና ብዛታቸውን እንደያዙ ከአሁኑ የቴክኖሎጂ ፈጣን ግስጋሴ ጋር እንዴት አብረው እንዲራመዱ ማድረግ ይቻላል? ለሚለው ጥያቄ ያገኘነው አማራጭ ዘመናትን ተሻግሮ ለኛ የደረሰንን ፊደልና ቋንቋ ከመቀየር ይልቅ ቴክኖሎጂውን ለአፃፃፋችን የተመቸ እንዲሆን ማድረግ ነው።

ዋና ዓላማችን ፊደሎቻችንን ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፉ የበኩላችንን ድርሻ ለማበርከት ስለሆነ ከሁሉም ፊደሎች ቢያንስ አንዱ በቁልፍ ሰሌዳው ላይ እንዲቀመጥ አድርገናል።   ለዚህም  ከበፊቱ ታይፕራይተር የትየባ ዘዴ እንዲሁም በላቲን ፊደሎች ላይ ተመርኩዘው ከሚፃፉት የቁልፍ ሰሌዳዎች በተለየ አዲስና ልዩ የራሳችን የሆነ የግዕዝ የቁልፍ ሰሌዳ ፈጥረናል።  የተቀሩትን ፊደሎች የያዘው ሙሉው የፊደል ገበታ ደግሞ በደስክ ቶፑ ላይ ሰፍሮ በቀላል መንገድ የፈለግነውን ፊደል እንድንጠቀም በሚያስችል መንገድ ተቀምጧል።

ቋንቋችንን ለመጠበቅ፣ለማሻሻልና ለማጎልበት አስፈላጊውን እርምጃ ከወሰድን ትምህርትን ለማስፋፋት፣ሃሳብን ለማንሸራሸር፣መረጃን በሰፊው ለማሰራጨት፣ እንዲሁም ባህላዊ እሴቶቻችንን፣ወግና ታሪካችን ለማሳወቅ ይረዳናል። ዘመኑ በፈጠረልን እጅግ ፈጣን የመግባቢያና የመልእክት ማሰራጫ ዘዴዎች በራሳችን ቋንቋ መገናኘትና መማማር ከቻልን እንግሊዝኛን ለመሳሰሉ አለም አቀፍ መግባቢያዎች ሙሉ በሙሉ እጃችንን ሰጥተን አገርኛ ቋንቋዎችን እንዳንጥል ይረዳናል ።

የኛ የፈጠራ ውጤት የግእዝን ፊደሎች የሚጠቀሙ ሁሉ በቀላሉ ለመፃፍ አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥርላቸው ቋንቋችንን ለማዳበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለን እናምናለን። አሁን በሰፊው እንደምናየው ወጣቶቻችን የተሻለ አማራጭ በማጣት በተወላገደና በተሳሳተ ፊደልና ቋንቋ መልእክት ሲለዋወጡ ይስተዋላል።  እንግሊዝኛ አይሉት አማርኛ በስህተት የተሞላ የተዳቀለ የመግባቢያ ፅሁፍ በየፌስቡክና አጫጭር የስልክ መልእክቶች ሲተላለፍ ታዝበናል።  ቋንቋችን አቡጊዳዊ (syllabary) ማለትም አናባቢንና ተነባቢን በአንድ ፊደል አጣምሮ የያዘ በመሆኑ የፊደል ግድፈት ወይም ስህተት ሳናደርግ መፃፋችን የምንኮራበት እሴታችን ነው። ይሁን እንጂ  በዘመናዊ መንገድ በቀላሉ የመፃፍ አማራጭ በማጣት የግዴለሽ አፃፃፍ እየተለመደ መጥቷል። በዚህ ከቀጠለ ከአባቶቻችን በጥንቃቄ ተጠብቆ የተረከብነው ቋንቋ ተከልሶና ተበርዞ ደብዛው ሊጠፋ ይችላል።  ቀስ በቀስ የመገናኛና በፅሁፍ የመግባቢያ ቋንቋችን የባዕድ ቋንቋዎች ሊሆኑ ነው። ይህንን ችግር ለመቅረፍ በኛ ለኛ የተሰራው ይህ ኮምፒውተር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለን እናምናለን።

በኢትዮፓስ ኮምፒውተሮቻችን አማካኝነት ባዘጋጀነው የቴክኒዎሎጂ ውጤት በመጠቀም በበኩላችን ፊደሎቹን መጠበቅ፣አስፈላጊነታቸውን ማስተጋባትና ቋንቋውም ለበለጠ ጥናትና መሻሻል ክፍት እንዲሆን ማድረግን ዋና ሥራችን አድርገነዋል። ለዚህም ጅምር ከናንተ ድጋፍን እንደምናገኝ ተስፋ እናደርጋለን።        

ይህ ያሁኑ የፈጠራ ውጤት በአይነቱ ፍፁም ልዩና ብቸኛ የሆነው የአማርኛ መተግበሪያና  አንድ ቁልፍ   በመጫን መፃፍ የሚያስችል የቁልፍ ሰሌዳ (Amharic hardware and software appliance)ስላለው ብቻ ሳይሆን ሌሎችም በርካታ ጥቅሞች አሉት።  ከነዚህም ጥቂቱን ለመዘርዘር

 • ላፕቶፑ  የተዘጋጀው በዩኒ ኮድ አጻጻፍ ዘዴ ስለሆነ የግእዝ ፊደላትን  በመጠቀም ያለ አንዳች ችግር በአማርኛ ኢሜይል ለመፃፍና በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ ለመጠቀም ያስችላል። ኢሜይል  የሚላክለት ሰው ተመሳሳይ ኮምፒውተር ባይኖረውም መልእክቱ በአማርኛ ያለ አንዳች ችግር ደርሶት ማንበብ ይችላል። በማንኛውም ኢሜይል አገልግሎት ሰጪ (ያሁ ጂሜይል ወይም ሌላ) ገፅ ላይ ተፅፎ የሚላክ መልእክት ብዙ ግዜ እንደሚያጋጥመው የተዘበራረቀ ፅሁፍ ወይም ትንንሽ ሳጥን መሰል ምልክቶች ሳይኖሩ በተቀባዩ በትክክል መነበብ ይችላል።
 • በግእዝ የፊደል ገበታ ላይ ከሚገኙት 233 ፊደሎች መካከል 60 ፊደሎች  በቀጥታ በቁልፍ ሰሌዳው  ( ኪቦርዱ ) ላይ ይገኛሉ።   ከሞክሼ ፊደላት በስተቀር ሁሉም የአማርኛ ፊደላት (ከሀ እስከ ፐ) በቁልፉ ሰሌዳ ላይ ይገኛሉ።
 • ሙሉው የፊደል ገበታ ደግሞ በደስክ ቶፑ ላይ ስለተጫነ በተፈለገ ጊዜ  ፊደሉ ላይ ክሊክ በማድረግ መፃፍ ይቻላል።።  
 • አማርኛና የግእዝ ፊደልን ተጠቃሚ ቋንቋዎችን ብቻ ሳይሆን የኩዌርቲ የቁልፍ ሰሌዳም ስላለው በላቲን ፊደል በሚጠቀሙ ቋንቋዎችም መፃፍ ይቻላል። አንድ ቁልፍ ብቻ በመንካት(ፊደል የሚለውን) የቁልፍ ሰሌዳውን ከአማርኛ ወደ ላቲን በመቀየር በእንግሊዝኛና በሌሎች የላቲን ፊደል ተጠቃሚ ቋንቋዎች መፃፍ ይቻላል።

      የፊደሎቹ አቀማመጥ

 • ከላይ እንደተገለፀው ላይ 60ዎቹ ፊደሎች በቁልፍ ሰሌዳው  ላይ እንዲሰፍሩ የተደረገው በአጠቃቀም ላይ ያላቸውን የድግግሞሽ መጠን ለማወቅ  ጥናት ከተደረገ በኋላ ነው። በጥናቱ መሰረት ድግግሞሻቸው ከፍተኛ የሆኑት ግዕዝ፣ራብዕና ሳድስ 48 ፊደሎች  ቅድሚያ ተሰጥቷቸው  በቁልፍ ሰሌዳው መሀል ላይ ሲቀመጡ 12 ሳድስ ፊደላት ደግሞ በስተግራ በኩል ቁጥራዊ የቁልፍ ሰሌዳ ላይ ተቀምጠዋል።  ከአ-ኦ ያሉትን አናባቢዎች በመጠቀም ሁሉንም ከግእዝ እስከ ሳብዕ ያሉትን ፊደላት መፃፍ ይቻላል። ይሁን እንጂ ዋናው አላማችን አንድ ቁልፍን ብቻ በመጫን ለመፃፍ መቻል ነው። ለዚህም ነው ላፕቶፑን ለመግለፅ ባለ አንድ ቁልፍ(One keystroke or mono touch) እንዲሁም ስብስብ (subset) የሚሉትን መገለጫዎች የምንጠቀመው።

ኮምፒውተሩና አጠቃቀሙ

 • 60 ፊደሎችና ሁለት የስርአተ ነጥብ ምልክቶች በቀጥታ   በቁልፍ      ሰሌዳው ( ኪቦርዱ ) ላይ ይገኛሉ።  አቀማመጣቸውም በሚከተለው ሁኔታ ነው።
 • 7  አናባቢዎች አኡኢኣኤእኦ  እንዲሁም  8ኛ ሆኖ የተቀመጠው  
 • አንድ ፊደል በሳብዕ  
 • 15 ፊደሎች በግዕዝ ለ መ ሰ ረ ቀ በ ተ ቸ ነ ከ ወ የ ደገ ጠ
 • 8 ፊደሎች በራብዕ  ላ ማ ራ ባ ታ ና ያ ጋ
 • 16 አንደኛ ደረጃ ተነባቢ ፊደሎች በሳድስ ህ ል ም ስ ር ቅ ብ ት ች ን ክ ው ይ ድ ግ ጥ
 • 12  ሁለተኛ ደረጃ ተነባቢ ፊደሎች በሳድስ ሽኝ ኽ ዝ ዥ ጅ ጭ ጵ ፅ ፍ ፕ ቭ
 • 2 ሥርዓተ ነጥቦች  ።  ፣

የ አ ምድብ (አናባቢዎች)

 • ከአ እስከ እ ያሉት ሰባቱ አናባቢ ፊደሎች የቁልፍ ሰሌዳችን ምሰሶዎች ናቸው። ለእያንዳንዱ ፊደል ከግዕዝ እስከ ሳብዕ ያለውን ሆሄ ለመፃፍ መጀመሪያ የ”አ”ን ቁልፍ ተጭነን ቀጥሎ ተፈላጊውን ፊደል መጫን ነው ። ለምሳሌ   አ + ለ = ለ    ኡ +ለ =ሉ

              ኢ+ ገ  = ጊ    እ + ወ =ው

 • በተመሳሳይ መንገድ “ኧ ” ን ና ተፈላጊውን ፊደል በመጫን ኋሏሟሷሯ ና የመሳሰሉትን እናገኛለን።  ኧ + ለ = ሏ    ኧ +ሰ =ሷ
 • ከአ እስከ ኦ ያሉትን ለመፃፍ ደግሞ የፊደሉን ቁልፍ(አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ) ሁለት ግዜ መጫን ብቻ  ነው ።
 • ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ተመሳሳይ ሆሄያት ያላቸውን ፊደሎች ከመካከላቸው አንዱ ብቻ ተመርጦ በቁልፍ ሰሌዳው ላይ እንዲቀመጥ ቢደረግም(ለምሳሌ ሰ ፅ ህ ) የአፃፃፍ ስርአቱ የሰመረ እንዲሆን  ሞክሼ ፊደላትን ጭምር የያዘው ሙሉው የፊደል ገበታ በደስክ ቶፑ ላይ ይገኛል።  በተፈለገ ጊዜ ከፊደል ገበታው ላይ ያለ ማንኛውም ፊደል ላይ ክሊክ በማድረግ መፃፍ ይቻላል። ስለዚህም ሞክሼዎቹን (እንደ ሐሠኀዐ ና ፀ የመሳሰሉትን) አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደስክ ቶፕ ላይ ከገኘው በህብረ ቀለም አማርኛ የሚለው ፅሁፍ ላይ ክሊክ ማድረግ ነው። ከዚያ ከአማርኛው የፊደል ገበታ ላይ በመጨለፍ (እላያቸው ላይ ክሊክ በማድረግ) ለመፃፍ ይቻላል። ለዚህ አሰራር የፊደል ገበታው ከሚፃፍበት ገፅ ጋር ጎን ለጎን ሆኖ እንዲቀመጥና ያለ ችግር መፃፍ እንዲቻል ተመቻችቶ ተዘጋጅቷል።

ተነባቢዎች

 • ከአናባቢዎቹ የአ ምድብ ፊደላት ቀጥሎ በቁልፍ ሰሌዳው ላይ ከተቀመጡት ፊደሎች አንዳንዶቹ ከሁለት በላይ ተመሳሳይ ሆሄያት አሏቸው(ለላል መማም ተታት)። ለእያንዳንዱ ፊደል  የተመደበለትን ቁልፉ በመጫን ራሱን ችሎ ከመፃፉ በተጨማሪ ከአ እስከ እ ያሉትን አናባቢዎች (ቫውልስ)  ከተጫኑ በኋላ ተፈላጊውን ፊደል ቀጥሎ በመንካት  ከግእዝ እስከ ሳብእ ያሉትን ፊደላት መፃፍ ይቻላል።
 • በተመሳሳይ መንገድ “ኧ ” ን ና ተፈላጊውን ፊደል በመጫን ኋሏሟሷሯ ና የመሳሰሉትን እናገኛለን።  ኧ+ሰ = ሷ   ኧ +መ = ሟ
 •  ከአ እስከ ኦ ያሉትን ለመፃፍ ደግሞ የፊደሉን ቁልፍ ሁለት ግዜ መጫን ብቻ     ነው ።
 • የቁልፍ ሰሌዳውን ከአማርኛ ወደ ላቲን ፊደል ለመቀየር ፊደል የሚለው ቃል የተፃፈበትን ቁልፍ በመጫን ብቻ በቀላሉ መቀየር ይቻላል።  ከላቲን ወደ አማርኛም እንደዚሁ።
 • የላቲን ቁጥሮችን ለመፃፍም ፊደል የሚለው ቃል የተፃፈበትን ቁልፍ በመጫን ብቻ ከአማርኛ ፊደል ወደ ቁጥር መለወጥና ከዚያም እንደገና ወደ አማርኛ ፊደል በቀላሉ መመለስ ይቻላል።
 • ከስርአተ ነጥቦች ነጠላ ሰረዝና (፣)ና አራት ነጥብ (።) ከቁጥራዊ ቁልፍ ሰሌዳ  ላይ ከግርጌ በኩል ተቀምጠዋል።
 • በላቲን እየተፃፈ በስሞል ሌተር የነበረውን ወደ ካፒታል ሌተር ለመለወጥ ሺፍትን መጫን  ብቻ ነው።  

 

With our innovation we stride a new path to the future

Our history and cultural heritage is rich and varied. It has shaped our identity and is a source of great national pride and international interest.

However, in this era of computers and internet, a language without an improved, simplified writing system is doomed to extinction.

As we can observe today, there is unsatisfactory Internet content written in Amharic and other local languages using the Ge’ez fidel. Books, dictionaries and other tools of learning on line are very limited.

To overcome this problem we want to contribute and are very proud to present to you our new laptop which gives native access to Ge’ez characters.

Our work, which took into account the importance of the proud history and heritage of the nation, will serve the Amharic language a useful purpose by providing the appropriate solution, a simple way of writing.  That is why we believe, that we have been successful in developing and implementing this very innovative computer with a unique and new Amharic keyboard.

Its software and architecture originated in the structural analysis we have made on the language itself. We have analyzed 11 million Amharic characters to get the most frequently used ones. Based on that, we have developed a method of rendering almost all Amharic characters on our unique keyboard. More precisely, we have selected a subset of characters which allows a very simplified writing system more easily manageable by children and young students. This subset is documented with an on line dictionary with various types of contents.

The subset does not exclude the complete set of Amharic characters and protects and promotes the syllabic specificity of this alphabet. The whole set of 233 characters can be displayed on the desktop

With our new state-of-the-art Amharic keyboard, most of the occurrences of the Ge’ez characters can be accessed with one key, as opposed to the combination usually needed on the Qwerty keyboard to write in Amharic and other Ge’ez alphabet using languages..

This new way of writing will foster the development of more effective educational materials based on the real language. We will propose a variety of tools for taking into account modern educational efforts.

To bring our modest contribution, we have a prepared a Review for the accumulation of contents in Amharic. It is a rich multimedia environment easily accessible to a world wide audience for maximum exposure.

Our work is dedicated to the preservation, promotion, study and development of the Amharic language through the use of this new technology provided on the Ethiopass computer. We also need to look at the language as a communication tool which can make on going changes with time. As the language evolves, the writing system can be improved following the evolution of the language. The present invention is directed towards ensuring the concept of writing in Amharic with a minimal number of key strokes. With a total breakaway from computers writing system attached to Latin characters, we have invented a unique independent Ethiopian keyboard. We believe that our innovation will solve the restrains of the Amharic language.

The absence of digital library facilities, and on line storage services to automatically back up valuable data, poor documentation and inadequate archive collections, are some of the shortcomings of the Amharic language in this era of mass communication. The lack of all these services has lead to the increasing demand for fast, accurate and easy access to good quality information.

If the necessary steps are carried out to improve, preserve and strengthen the Amharic language, it can serve to disseminate ideas and to promote the values, traditions, history, and culture which Ethiopia embodies and symbolizes.

As it can clearly observed the Ge’ez alphabet is cluttered with different letters for superfluous repetition and overlapping sounds. As a result, Amharic writing is mired by too many redundant letters for identical sounds, for example ሀ ሐ ኀ ሃሓ ኃ ኻ, all representing the sound ”Ha”.

In our new approach to resolve the problem, emphasis is given to the survival and continued development of our language, by making it a vehicle for real life communication. We believe that it will be a great support to resist the invasion of major international Internet languages, like English.

Our computers provide the first one-key Amharic hardware and software appliance. To cite only some of their numerous advantages:

 • Support of email communication and surfing on the Internet in Amharic.
 • Efficient by expanding the keyboard for use of all Amharic characters.
 • The complete fidel table with all characters can be displayed on the desktop. If the need arises, one can insert every character by double clicking on the alphabet, and this from within any application.
 • It is Compatible with Qwerty keyboards. It is very easy to switch from Amharic into English with just one stroke on the ፊደል(Caps lock) key.

Display of the keyboard

As a result of our study, the most frequently used 60 fidels are displayed on the keyboard.

Most of them (48) are consonants from the 1st, 4th and 6th orders. Then we have 12 other fidels again from the 6th order. All seven orders of each character can be obtained by striking any of the characters with the vowels አ-ኦ and the diphthongs in combination with. The important part is with the most frequently used characters being in the 6th order, all are represented on the right side of the keyboard. This enables the user to write with one keystroke, which we call mono touch.

How to use the computer

60 characters and 2 punctuation marks are on the keyboard. The keyboard is organized in the following manner:

 • 7+1 Vowels, አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ ኧ Seven vowels and one exception()
 • 1 fidel from the 7th order
 • 15 fidels from the 1st order ለ መ ሰ ረ ቀ በ ተ ቸ ነ ከ ወ የ ደገ ጠ
 • 8 fidels from the 4th order ላ ማ ራ ባ ታ ና ያ ጋ
 • 16 primary consonants from the 6th order ህ ል ም ስ ር ቅ ብ ት ች ን ክ ው ይ ድ ግ ጥ
 • 12 secondary consonants from the 6th order ሽኝ ኽ ዝ ዥ ጅ ጭ ጵ ፅ ፍ ፕ ቭ
 • Two punctuation marks ። and ፣

The አ column- Vowels

On the left side of the keyboard, on two rows, we have the vowels አ-ኦ and an exceptionኧ.

These vowels are used to obtain:

 • The seven orders of any character on the keyboard
  Ex አ + ለ = ለ  ኡ +ለ =ሉ    ኢ+ ገ  = ጊ   እ + ወ =ው
 • The exceptions like ሏ ሟ ሷ   by combining ኧ with the appropriate character, E.g  ኧ+ሰ = ሷ   ኧ +መ = ሟ
 • አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ by double striking the same key.
 • The whole Amharic fidel can be displayed on the desktop and is accessible by a double click on any given character if the need arises to use some of the double characters like ሐ, ሠ, ኀ, ዐ or ጸ.

Consonants

 • Next to the vowels are displayed the consonants from the 1st, 4th and 6th orders. The characters are engraved on the keyboard in such a way that some of them are displayed more than twice.  (ለልላ መማም  ተታት ). All seven orders of each character could be obtained by striking any of the characters with the vowels አ-ኦ.
 • In the same manner, the exceptions like ሏ ሟ ሷ could be obtained by combining ኧ with the appropriate character
  E.g  ኧ+ሰ = ሷ   ኧ +መ = ሟ
 • አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ by double striking the same key.
 • One stroke on the Caps lock key(ፊደል), will get us back to the Latin alphabets.
 • Punctuation marks ። ፣ are on the last row of the numerical keypad.

Get your amharic laptop now

A powerful Fujitsu with an amharic keyboardThis FUJITSU Notebook LIFEBOOK A555G is a high-end laptop designed for nomad everyday work.


Its Intel® CoreTM i5-5200U processor is the fifth generation of Intel chips, specifically created to reduce the energy consumption of the device. You can work longer while on battery with no drop in the overall performance of your applications.


It comes with an AMD RadeonTM R7 M260 graphics card with 2GB dedicated memory, enabling full HD display for an optimal visual rendition.


You will experience no shortage of memory with its 4GB RAM, and 1TB Hard Disk Drive memory.


This great hardware runs a customised version of Ubuntu, enabling for full support of both English and Amharic languages.


Facebook
Special offer!

Subscribe to our newsletter